የጥያቄና መልስ ውድድር በአጋር ት/ቤቶች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ተካሄደ

የጥያቄና መልስ ውድድር በአጋር ት/ቤቶች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ተካሄደ

ውድድሩ በሁለቱም ክፍለ ከተሞች ላይ የተካሄደ ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች በአባዶ ትምህርት ቤት ላይ እንዲሁም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች መካከል በፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ላይ የተካሄደ ሲሆን ከየካ ክፍለ ከተማ ተማሪ ረድኤት እድሉ ከአባዶ ት/ቤት አንደኛ ስትወጣ ተማሪ እሰተ ይመር ከኮተቤ ብርሃነ ህይወት ሁለተኛ ወጥታለች፡፡ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ደግሞ ተማሪ እዮቤድ ተክሌ ከየማነ ብርሃን ት/ቤት አንደኛ ሲወጣ ተማሪ ሔርሜላ ኤፍሬም ከአስኮ አዲስ ሰፈር ት/ቤት ደግሞ ሁለተኛ ወጥታለች፡፡ ውድድሩ ከየትምህርት ቤቱ በተወከሉ ሁለት ሁለት በአጠቃላይ 16 ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን እነዚህ በሁለቱም ክፍለ ከተሞች አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡት አራት ተማሪዎች ከአንደኛ ሴሚስተር ፈተና በኋላ ክፍለ ከተሞቻቸውን ወክለው የአሸናፊዎች አሸናፊ የማጠቃለያ ውድድር በንጋት ኮከብ ት/ቤት ላይ ያካሂዳሉ፡፡

በውድድሩም ከ 1ኛ – 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች እንደየደረጃቸው ሽልማትና ሰርተፊኬት የተበረከተላቸው ሲሆን ለሌሎች ተሳታፊ ተማሪዎች እና ለሁሉም አጋር ት/ቤቶች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም ውድድር በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የፍክክር መንፈስ ለመፍጠር የተቻለ ሲሆን ይህም ለወደፊቱ በጥናታቸው እና በውጤታቸው መሻሻል ላይ አዎንታዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይታሰባል፡፡ 

ውድድሩን ያዘጋጁት የአባዶና የፊታውራሪ ሀ/ጊዮርጊስ ት/ቤቶች ከፍ ያለ ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

shares